4 እነሆ፤ እርሱን ለሕዝቦች ምስክር፣መሪ፣ የጦር አዝማችም አድርጌዋለሁ።
5 እነሆ፤ የማታውቃቸውን መንግሥታት ትጠራለህ፤የማያወቁህ መንግሥታት በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ፤ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክህ፣የእስራኤል ቅዱስ፣በክብሩ ከፍ ከፍ አድርጎሃል።
6 እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ቀርቦም ሳለ ጥሩት።
7 ክፉ ሰው መንገዱን፣በደለኛም ሐሳቡን ይተው።ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።
8 “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”ይላል እግዚአብሔር።
9 “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።
10 ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ምድርን በማራስ፣እንድታበቅልና እንድታፈራለዘሪው ዘር፣ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣