5 እነሆ፤ የማታውቃቸውን መንግሥታት ትጠራለህ፤የማያወቁህ መንግሥታት በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ፤ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክህ፣የእስራኤል ቅዱስ፣በክብሩ ከፍ ከፍ አድርጎሃል።
6 እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ቀርቦም ሳለ ጥሩት።
7 ክፉ ሰው መንገዱን፣በደለኛም ሐሳቡን ይተው።ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።
8 “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”ይላል እግዚአብሔር።
9 “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።
10 ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ምድርን በማራስ፣እንድታበቅልና እንድታፈራለዘሪው ዘር፣ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣
11 ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።