12 በደላችን በፊትህ በዝቶአል፤ኀጢአታችን መስክሮብናል፤በደላችን ከእኛ አልተለየም፤ዐመፀኝነታችንንም እናውቃለን።
13 በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።
14 ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ጽድቅም በሩቁ ቆሞአል፤እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሎአል፤ቅንነትም መግባት አልቻለም።
15 እውነት የትም ቦታ አይገኝም፤ከክፋት የሚርቅ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ተመለከተ፤ፍትሕ በመታጣቱም ዐዘነ።
16 ማንም እንደሌለ አየ፤ወደ እርሱ የሚማልድ ባለመኖሩ ተገረመ፤ስለዚህ የገዛ ክንዱ ድነት አመጣለት፤የራሱም ጽድቅ ደግፎ ያዘው።
17 ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤የድነትን ቊር በራሱ ላይ ደፋ፤የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ።
18 እንደ ሥራቸው መጠን፣ቊጣን ለባላጋራዎቹ፣ፍዳን ለጠላቶቹ፣እንደዚሁ ይከፍላቸዋል፤ለደሴቶችም የእጃቸውን ይሰጣቸዋል።