ኢሳይያስ 59:6-12 NASV

6 ድሮቻቸው ልብስ አይሆኑም፤በሚሠሩትም ሰውነታቸውን መሸፈን አይችሉም፤ሥራቸው ክፉ ነው፤እጃቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞላ ነው።

7 እግሮቻቸው ወደ ኀጢአት ይሮጣሉ፤ንጹሕ ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤የሚያስቡት ክፉ ሐሳብ ነው፤ማጥፋትና ማፈራረስም የመንገዳቸው ምልክት ነው።

8 የሰላምን መንገድ አያውቁም፤በጐዳናቸውም ፍትሕ የለም፤መንገዳቸውን ጠማማ አድርገውታል፤በዚያም የሚሄድ ሰላም አያገኝም።

9 ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ጽድቅም ወደ እኛ አይመጣም፤ብርሃንን ፈለግን፤ ነገር ግን ሁሉ ጨለማ ነው፤የብርሃንን ጸዳል ፈለግን፤ የምንሄደው ግን በድንግዝግዝታ ነው።

10 በቅጥሩ ላይ እንደ ዕውር ተደናበርን፤አካሄዳችንም ዐይን እንደሌላቸው በዳበሳ ሆነ፤ጀምበር በምትጠልቅበት ጊዜ እንደሚሆነው በእኩለ ቀን ተደናበርን፤በብርቱዎች መካከልም እንደ ሙታን ሆንን።

11 ሁላችን እንደ ድቦች እናላዝናለን፤እንደ ርግቦችም በመቃተት እንጮኻለን፤ፍትሕን ፈለግን፤ ግን አላገኘንም፤ትድግናን ፈለግን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቆአል።

12 በደላችን በፊትህ በዝቶአል፤ኀጢአታችን መስክሮብናል፤በደላችን ከእኛ አልተለየም፤ዐመፀኝነታችንንም እናውቃለን።