ኢሳይያስ 6:5-11 NASV

5 እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።

6 ከዚያም ከሱራፌል አንዱ፣ ከመሠዊያው ላይ የእሳት ፍም በጒጠት ወስዶ፣ ወደ እኔ እየበረረ መጣ።

7 አፌንም በእሳቱ ነክቶ፣ “እነሆ፤ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኀጢአትህም ተሰርዮልሃል” አለኝ።

8 ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት።እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” አልሁ።

9 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤“ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።

10 የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ጆሮአቸውን ድፈን፤ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ይህ ካልሆነማ፣በዐይናቸው አይተው፣ በጆሮአቸው ሰምተው፣በልባቸውም አስተውለውበመመለስ ይፈወሳሉ።”

11 እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤“ከተሞች እስኪፈራርሱና፣የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፣ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤