1 “ብርሃንሽ መጥቶአልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል።
2 እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ክብሩንም ይገልጥልሻል።
3 ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ።
4 “ቀና በዪ፤ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ሁሉም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ፣ሴቶች ልጆችሽም በዕቅፍ ወደ አንቺ ይመጣሉ።
5 ከዚያም ታያለሽ፤ ታብረቀርቂያለሽ፤ልብሽ ይዘላል፤ በደስታም ይሞላል።በባሕሮች ያለው ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል፤የነገሥታትም ብልጥግና የአንቺ ይሆናል።