4 ከእንግዲህ፣ “የተተወች” ብለው አይጠሩሽም፤ምድርሽም፣ “የተፈታች” አትባልም፤ነገር ግን፣ “ደስታዬ በእርሷ” ትባያለሽ፤ምድርሽም፣ “ባለ ባል” ትባላለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ምድርሽም ባለ ባል ትሆናለች።
5 ጐልማሳ ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ልጆችሽ እንዲሁ ያገቡሻል፤ሙሽራ በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፣አምላክሽም በአንቺ ደስ ይለዋል።
6 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም።እናንት ወደ እግዚአብሔር አቤት፣ አቤት የምትሉ፤ፈጽሞ አትረፉ፤
7 ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት፣የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ዕረፍት አትስጡት።
8 እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሎአል፤“ከእንግዲህ እህልሽን፣ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።
9 ነገር ግን መከሩን የሰበሰቡ ይበሉታል፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፤የወይኑን ፍሬ የለቀሙም በመቅደሴአደባባዮች ይጠጡታል።”
10 ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ፤ድንጋዩን አስወግዱ፤ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ።