1 ይህ ከኤዶም፣ቀይ የተነከረ መጐናጸፊያ ለብሶ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው?ይህ ክብርን የተጐናጸፈ፣በኀይሉ ታላቅነት እየተራመደ የሚመጣውስ ማን ነው?“በጽድቅ የምናገር፣ለማዳንም ኀይል ያለኝ እኔው ነኝ።”
2 መጐናጸፊያህ፣ ለምንበወይን መጭመቂያ ወይን እንደሚረግጡ ሰዎች ልብስ ቀላ?
3 “እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋር አልነበረም፤በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቶአል፤ልብሴንም በክዬዋለሁ።
4 የበቀል ቀን በልቤ አለ፤የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአል።
5 ተመለከትሁ፤ የሚረዳ ግን አልነበረም፤የሚያግዝ ባለመኖሩም ተገረምሁ፤ስለዚህ የገዛ ክንዴ ድነትን አመጣልኝ፤የገዛ ቊጣዬም አጸናኝ፤