ኢሳይያስ 65:1-7 NASV

1 “ላልለመኑኝ ራሴን ገለጥሁላቸው፤ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው።ስሜን ላልጠራ ሕዝብ፣‘አለሁልህ፤ አለሁልህ’ አልሁት።

2 ለዐመፀኛ ሕዝብ፣መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ።ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣

3 በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤

4 በመቃብር መካከል የሚቀመጡ፣በስውር ቦታዎች የሚያድሩ፣የዕሪያ ሥጋ የሚበሉ፣ማሰሮዎቻቸውን በረከሰ ሥጋ መረቅ የሚሞሉ ናቸው፤

5 ‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ’ የሚሉ ናቸው።እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።

6 “እነሆ፤ እንዲህ የሚል ተጽፎ በፊቴ ተቀምጦአል፤ዝም አልልም፤ ነገር ግን እንደ ሥራው እሰጠዋለሁ፤የእጃቸውንም እከፍላቸዋለሁ፤

7 የእናንተን ኀጢአት የአባቶቻችሁንም ኀጢአት እበቀላለሁ”ይላል እግዚአብሔር።“በተራሮች ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ስላቀረቡ፣በኰረብቶች ላይ ስለ ሰደቡኝ፣በሰፈሩት ቊና ይሰፈርባቸዋል፤ስለ ቀደሙት ሥራዎቻቸውም የእጃቸውን ያገኛሉ።”