ኢሳይያስ 66:11-17 NASV

11 ከሚያጽናኑ ጡቶቿ፣ትጠባላችሁ፤ ትረካላችሁም፤እስክትረኩም ትጠጣላችሁ፤በተትረፈረፈ ሀብቷም ትደሰታላችሁ።”

12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ ሰላምን እንደ ወንዝ ውሃ አፈስላታለሁ፤የመንግሥታትንም ብልጥግና እንደ ጅረት ውሃ አጐርፍላታለሁ፤ትጠባላችሁ፤ በዕቅፏም ትያዛላችሁ፤በጭኖቿም ላይ ትፈነድቃላችሁ።

13 እናት ልጇን እሹሩሩ እንደምትል፣እኔም እናንተን እሹሩሩ እላችኋለሁ፤በኢየሩሳሌምም ትጽናናላችሁ።

14 ይህን ስታዩ፣ ልባችሁ ሐሤት ያደርጋል፤ዐጥንቶቻችሁም እንደ ሣር ይለመልማሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ከባሮቹ ጋር መሆኑ ይታወቃል፤ቊጣው ግን በጠላቶቹ ላይ ይገለጣል።

15 እነሆ፤ እግዚአብሔር በእሳት ነበልባል ይመጣል፤ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ንዴቱን በቍጣ፣ተግሣጹንም በእሳት ነበልባል ይገልጣል።

16 በእሳትና በሰይፍ፣ እግዚአብሔር ፍርዱን በሰው ሁሉ ላይ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር ሰይፍ የሚታረዱት ብዙ ይሆናሉ።

17 “ወደ አትክልት ቦታዎች ለመሄድና ከተክሎቹ አንዱን ለማምለክ ራሳቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የዕሪያዎችንና የዐይጦችን ሥጋ፣ የረከሱ ነገሮችንም የሚበሉ ሁሉ የመጨረሻ ፍርዳቸውን በአንድነት ይቀበላሉ” ይላል እግዚአብሔር።