ዘሌዋውያን 6:17-23 NASV

17 ያለ እርሾ መጋገር አለበት፤ በእሳት ከሚቀርብልኝ ቊርባን ይህን የእነርሱ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። ይህም፣ እንደ ኀጢአት መሥዋዕትና እንደ በደል መሥዋዕት ሁሉ እጅግ የተቀደሰ ነው።

18 ማንኛውም ከአሮን ዘር የተወለደ ወንድ ሊበላው ይችላል፤ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከሚቀርበው የእሳት ቍርባን ለእርሱ የተመደበ የዘላለም ድርሻው ነው፤ የሚነካውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’ ”

19 እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

20 “አሮን ወይም ልጆቹ በተቀቡበት ዕለት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያቀርቡት ቊርባን ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ ዐሥረኛው የላመ ዱቄት ግማሹን ለጧት፣ ግማሹን ለማታ የዘወትር የእህል ቊርባን አድርገው ያቅርቡት።

21 በሚገባ በዘይት ተለውሶ በምጣድ ላይ ይጋገር፤ ከዚያም የእህሉን ቊርባን ቈራርሰህ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ አቅርብ።

22 በእርሱ ቦታ ተቀብቶ ካህን የሚሆነው ልጁ ይህን ያዘጋጅ፤ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተመደበ ድርሻ ነውና ፈጽሞ ይቃጠል።

23 ካህኑ የሚያቀርበው የእህል ቊርባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃጠል እንጂ አይበላ።”