15 እኔ፣ እኔው ራሴ ተናግሬአለሁ፤በርግጥ እኔ ጠርቼዋለሁ፤አመጣዋለሁ፤ሥራውም ይከናወንለታል።
16 “ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤“ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።”አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱልከውኛል።
17 የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣የሚበጅህ ምን እንደሆነ የማስተምርህ፣መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።
18 ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።
19 ዘርህ እንደ አሸዋ፣ልጆችህ ስፍር እንደሌለው ትቢያ በሆኑ ነበር፤ስማቸው አይወገድም፤ከፊቴም አይጠፋም።
20 ከባቢሎን ውጡ፣ከባቢሎናውያንም ሽሹ!ይህን በእልልታ አስታውቁ፤ ዐውጁት፤እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተናገሩ፤“እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብንተቤዥቶታል” በሉ።
21 በምድረ በዳ ሲመራቸው አልተጠሙም ነበር፤ውሃ ከዐለት አፈለቀላቸው፤ዐለቱን ሰነጠቀ፤ውሃውም በኀይል ፈልቆ ወጣ።