2 በቅንነት የሚሄዱ፣ሰላም ይሆንላቸዋል፤መኝታቸው ላይ ያርፋሉ።
3 “እናንት የአስማተኛዪቱ ልጆች ግን፣እናንት የአመንዝራውና የጋለሞታዪቱ ዘር፤ እናንት፣ ወዲህ ኑ፤
4 የምትሣለቁት በማን ላይ ነው?የምታሽሟጥጡት ማንን ነው?ምላሳችሁንስ አውጥታችሁ የምታሾፉት በማን ላይ ነው?እናንት የዐመፀኞች ልጆች፣የሐሰተኞች ዘር አይደላችሁምን?
5 በባሉጥ ዛፎች መካከል፣ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሥር በዝሙት የምትቃጠሉ፣በሸለቆዎች፣ በዐለት ስንጣቂዎችም ውስጥልጆቻችሁን የምትሠዉ አይደላችሁምን?
6 በሸለቆው በሚገኙት ለስላሳ ድንጋዮችውስጥ ያሉት ጣዖቶች የአንቺ ናቸው፤እነርሱም ዕጣ ፈንታዎችሽ ናቸው፤ርግጥ ነው፣ በእነርሱ ላይ የመጠጥ ቊርባን አፍስሰሻል፤የእህል ቍርባንም አቅርበሻል፤ታዲያ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዝም እላለሁን?
7 ዐልጋሽን ከፍ ባለውና በረጅሙ ኰረብታ ላይ አነጠፍሽ፤በዚያም መሥዋዕትሽን ልታቀርቢ ወጣሽ።
8 ከመዝጊያሽና ከመቃንሽ ጀርባ፣የጣዖት ምስሎችሽን ሰቀልሽ፤እኔን ትተሽ መኝታሽን ገላለጥሽ፤በላይም ወጥተሽ በጣም ገለጥሽው፤መኝታቸውን ከወደድሽላቸው ጋር ስምምነት አደረግሽ፤ዕርቃናቸውንም አየሽ።