1 አቤቱ፤ ሰማያትን ቀድደህ ምነው በወረድምነዋ ተራሮች በፊትህ በተናወጡ
2 እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ውሃንም እንደሚያፈላ፣ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ።
3 እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።
4 ከጥንት ጀምሮ፣በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣እንደ አንተ ያለውን አምላክ ያየ ዐይን፣ያደመጠ ጆሮ ፈጽሞ አልነበረም።
5 በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣እነሆ፣ ተቈጣህ፤ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን?