ኢሳይያስ 64:2-8 NASV

2 እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ውሃንም እንደሚያፈላ፣ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ።

3 እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።

4 ከጥንት ጀምሮ፣በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣እንደ አንተ ያለውን አምላክ ያየ ዐይን፣ያደመጠ ጆሮ ፈጽሞ አልነበረም።

5 በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣እነሆ፣ ተቈጣህ፤ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን?

6 ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።

7 ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል።

8 ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤