15 ሞዓብ ትጠፋለች፤ ከተሞቿም ይወረራሉ፤ምርጥ ወጣቶቿም ወደ መታረድ ይወርዳሉ፤”ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ፤
16 “የሞዓብ ውድቀት ተቃርቦአል፤ጥፋቱም ፈጥኖ ይመጣበታል።
17 በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤‘ብርቱው ከዘራ፣የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ።
18 “ሞዓብን የሚያጠፋ፣በአንቺ ላይ ይመጣልና፤የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፣ከክብርሽ ውረጂ፣በደረቅም መሬት ተቀመጪ።
19 አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።
20 ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤የሞዓብን መደምሰስ፣በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።
21 ፍርድ በዐምባው ምድር፦በሖሎን፣ በያሳና በሜፍዓት ላይ፣