ኤርምያስ 47 NASV

ስለ ፍልስጥኤማውያን የተነገረ መልእክት

1 ፈርዖን ጋዛን ድል ከማድረጉ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፣ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል።ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤

3 ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና፣ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።

4 ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ቀኑ ደርሶአልና። እግዚአብሔር በከፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋተነሥቶአል።

5 ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፣አስቀሎና አፏን ትይዛለች።በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ትሩፋን ሆይ፤እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?

6 “ ‘የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፤የማታርፈው እስከ መቼ ነው?ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።

7 ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣እንዲወጋ ሲያዝዘው፣እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣እንዴት ማረፍ ይችላል?”

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36 37 38 39 40 41 42 43 44 45 46 47 48 49 50 51 52