18 “ሞዓብን የሚያጠፋ፣በአንቺ ላይ ይመጣልና፤የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፣ከክብርሽ ውረጂ፣በደረቅም መሬት ተቀመጪ።
19 አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።
20 ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤የሞዓብን መደምሰስ፣በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።
21 ፍርድ በዐምባው ምድር፦በሖሎን፣ በያሳና በሜፍዓት ላይ፣
22 በዲቦን፣ በናባውና በቤት ዲብላታይም ላይ፣
23 በቂርያታይም፣ በቤት ጋሙልና በቤትምዖን ላይ፣
24 በቂርዮትና በባሶራ ላይ፤በሩቅና በቅርብ፣ ባሉት በሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቶአል።