10 “ ‘እናትህ በውሃ አጠገብ የተተከለ፣በዕርሻ ውስጥ ያለ፣ከውሃም ብዛት የተነሣ፣ያፈራና የተንሰራፋ የወይን ተክልመሰለች።
11 ቅርንጫፎቿ ለበትረ መንግሥትየሚሆኑ፣ ጠንካሮች ነበሩ፤ጥቅጥቅ ባሉ ቅጠሎች መካከል፣በቁመቷና በብዙ ቅርንጫፎቿ፣ዘለግ ብላ፣ ጐልታ ትታይ ነበር።
12 ነገር ግን በቍጣ ተነቀለች፤ወደ ምድርም ተጣለች።የምሥራቅ ነፋስ አደረቃት፤ፍሬዎቿንም አረገፈባት።ብርቱዎቹ ቅርንጫፎቿ ክው አሉ፤እሳትም በላቸው።
13 አሁን ውሃ በተጠማ ደረቅ ምድር፣በበረሓ ውስጥ ተተከለች።
14 ከዋና ቅርንጫፎቿ ከአንዱ እሳት ወጣ፤ፍሬዋንም በላ።በትረ መንግሥት የሚሆን፣አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ አልተረፈም።’ይህ ሙሾ ነው፤ ለሐዘን እንጒርጒሮም ይሆናል።’