4 አሕዛብም ስለ እርሱ ሰሙ፤በጒድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ፤እነርሱም በስናግ ጐትተው፣ወደ ግብፅ ምድር ወሰዱት።
5 “ ‘ተስፋዋ መጨናገፉን፣የጠበቀችውም አለመሳካቱን ባየች ጊዜ፣ከግልገሎቿ ሌላውን ወስዳ፣ብርቱ አንበሳ አድርጋ አሳደገችው።
6 እርሱም በአንበሶች መካከል ተጐማለለ፤እየበረታም ሄደ፤ግዳይ መንጠቅን ተማረሰዎችንም በላ።
7 ምሽጎቻቸውን አወደመ፤ከተሞቻቸውንም ባድማ አደረገ፤ምድሪቷና በውስጧ ያሉት ሁሉ፣ከግሣቱ የተነሣ ተንቀጠቀጡ።
8 በዙሪያው ያሉ አሕዛብ ተነሡበት፤ከየአገሩም ሁሉ ተሰበሰቡበት፤መረባቸውን ዘረጉበት፤በጒድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ።
9 በስናግም በመጐተት ቀፎ ውስጥ ከተው፣ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ፣ዳግመኛ እንዳይሰማ፣በእስር ቤት አኖሩት።
10 “ ‘እናትህ በውሃ አጠገብ የተተከለ፣በዕርሻ ውስጥ ያለ፣ከውሃም ብዛት የተነሣ፣ያፈራና የተንሰራፋ የወይን ተክልመሰለች።