28 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ ተጸይፈሻቸው ከእነርሱ ዘወር ላልሽው ለጠላሻቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ።
29 እነርሱም በጥላቻ ይቀርቡሻል፤ የለፋሽበትንም ሁሉ ይቀሙሻል፤ ከማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ያስቀሩሻል፤ የሴሰኝነትሽ ኀፍረት ይገለጣል። ብልግናሽና ገደብ የለሽ ርኵሰትሽ፣
30 ይህን አምጥተውብሻል፤ ከአሕዛብ ጋር በማመንዘር በጣዖቶቻቸው ረክሰሻልና።
31 በእኅትሽ መንገድ ስለ ሄድሽ የእርሷን ጽዋ በእጅሽ አስጨብጥሻለሁ።’
32 “ጌታእግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሰፊና ጥልቅ የሆነውን ጽዋ፣የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ብዙም ስለሚይዝ ስድብና ነቀፌታትጠግቢአለሽ።
33 በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፣በመፍረስና በጥፋት ጽዋ፣በስካርና በሐዘን ትሞዪአለሽ።
34 ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።