8 ቍጣዬ እንዲነድና ለመበቀል እንዲያመቸኝ፣ይሸፈንም ዘንድ እንዳይችል፣ደሟን በገላጣ ዐለት ላይ አፈሰስሁ።
9 “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት!እኔም ደግሞ የምትቃጠልበትን ማገዶ እቈልላለሁ።
10 ማገዶውን ከምርበት፤እሳቱን አንድድ፤ቅመም ጨምረህበት፣ሥጋውን በሚገባ ቀቅል፤ዐጥንቱም ይረር።
11 ጒድፉ እንዲቀልጥ፣ዝገቱም በእሳት እንዲበላ፣ባዶው ድስት እስኪሞቅ፣መደቡም እስኪግል ከሰል ላይ ጣደው።
12 ብዙ ጒልበት ቢፈስበትም፣የዝገቱ ክምር፣በእሳት እንኳ፣ ሊለቅ አልቻለም።
13 “ ‘የረከስሽው በብልግናሽ ነው፤ ቍጣዬ በአንቺ ላይ እስኪፈጸም ድረስ ከእንግዲህ ንጹሕ አትሆኚም፤ ከርኵሰትሽ ላነጻሽ ፈልጌ፣ መንጻት አልወደድሽምና።
14 “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ የምሠራበትም ጊዜ ደርሶአል፤ ወደ ኋላ አልልም፤ አልራራም፤ አላመነታምም። እንደ መንገድሽና እንደ ተግባርሽ ይፈረድብሻል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”