ሕዝቅኤል 28:18-24 NASV

18 በኀጢአትህና በተጭበረበረው ንግድህ ብዛት፣መቅደስህን አረከስህ።ስለዚህ እሳት ከአንተ እንዲወጣ አደረግሁ፤እርሱም በላህ፤በሚመለከቱህ ሁሉ ፊት፣በምድር ላይ ዐመድ አደረግሁህ።

19 የሚያውቁህን አሕዛብ ሁሉ፣ሁኔታህ አስደንግጦአቸዋል፤መጨረሻህ የሚያሳዝን ሆነ፤ከእንግዲህ ሕልውና የለህም።

20 የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

21 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ሲዶና አዙር፤ ትንቢትም ተናገርባት፤

22 እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ሲዶን ሆይ፤ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤በውስጥሽ እከብራለሁ፤ቅጣትን ሳመጣባት፣ቅድስናዬንም በውስጧ ስገልጥ፣እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

23 በእርሷ ላይ መቅሠፍት አመጣለሁ፤በመንገዶቿ ላይ ደም እንዲፈስ አደርጋለሁ፤ከየአቅጣጫው በሚመጣ ሰይፍ፣የታረዱት በውስጧ ይወድቃሉ፤ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

24 “ ‘ከእንግዲህ ወዲያ የእስራኤል ሕዝብ የሚያሠቃይ አሜከላና የሚወጋ እሾኽ የሆኑ ጎረቤቶች አይኖሯቸውም፤ ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።