1 የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤“ወዮ ለዚያ ቀን!”
3 ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤የደመና ቀን፣ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።
4 በግብፅ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል።የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ሀብቷ ይወሰዳል፤መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።