ሕዝቅኤል 31:7-13 NASV

7 ከተንሰራፉት ቅርንጫፎቹ ጋር፣ውበቱ ግሩም ነበር፤ብዙ ውሃ ወዳለበት፣ሥሮቹ ጠልቀው ነበርና።

8 በእግዚአብሔር ገነት ያሉ ዝግባዎች፣ሊወዳደሩት አልቻሉም፤የጥድ ዛፎች፣የእርሱን ቅርንጫፎች አይተካከሉትም፤የአስታ ዛፎችም፣ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር አይወዳደሩም፤በእግዚአብሔር ገነት ያለ ማናቸውም ዛፍ፣በውበት አይደርስበትም።

9 በብዙ ቅርንጫፎች፣ውብ አድርጌ ሠራሁት፤በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ፣በገነት ያሉትን ዛፎች የሚያስቀና አደረግሁት።

10 “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥቅጥቅ ባለው ቅጠል ላይ ጫፉን ከፍ በማድረግ ራሱን በማንጠራራቱ፣ በርዝማኔውም በመኵራራቱ፣

11 እንደ ክፋቱ መጠን የሥራውን ይከፍለው ዘንድ፣ ለአሕዛብ ገዥ አሳልፌ ሰጠሁት። አውጥቼ ጥየዋለሁ፤

12 ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተውት ሄደዋል።

13 የሰማይ ወፎች ሁሉ በወደቀው ዛፍ ላይ ሰፈሩ፤ የምድር አራዊት ሁሉ በወደቀው ዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ሰፈሩ።