ሕዝቅኤል 35:5-11 NASV

5 “ ‘እስራኤላውያን ቅጣታቸው እጅግ መራራ ከሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ፍዳቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ፣ የጥንቱን ቂም ቋጥረህ ለሰይፍ ስለ ዳረግሃቸው፤

6 በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ለደም ማፍሰስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ እርሱም ያሳድድሃል። ደም ማፍሰስን ስላልጠላህ፣ ደም ማፍሰስ ያሳድድሃል።

7 የሴይርን ተራራ ባድማና ጠፍ አደርጋለሁ፤ በእርሱም ላይ የሚወጡትንና የሚወርዱትን አስቀራለሁ።

8 ተራሮችህን በሬሳ እሞላለሁ፤ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ በተራሮችህ፣ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ ይወድቃሉ።

9 ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህ መኖሪያ አይሆኑም። ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

10 “ ‘እኔ እግዚአብሔር በዚያ እያለሁ፣ “እነዚህ ሁለት ሕዝቦችና ሁለት አገሮች የእኛ ይሆናሉ፤ እኛም እንወርሳቸዋለን።” ብለሃልና፤

11 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከጥላቻችሁ የተነሣ በእነርሱ ላይ በገለጣችሁት ቍጣና ቅናት ልክ እፈርድባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ፣ ማንነቴ በእነርሱ መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ።