ሕዝቅኤል 48:4-10 NASV

4 “የምናሴ ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የንፍታሌምን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።

5 “የኤፍሬም ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የምናሴን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።

6 “የሮቤል ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የኤፍሬምን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።

7 “የይሁዳ ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የሮቤልን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።

8 “ይሁዳን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚያዋስነው ምድር ለመባ የሚቀርብ ድርሻ ይሆናል፤ ስፋቱም ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ነው፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውም ርዝመቱ፣ ከነገዶቹ ድርሻ እንደ አንዱ ሆኖ፣ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።

9 “ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የዚህ መባ ርዝመት ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ሲሆን፣ ስፋቱ ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል።

10 ይህ ለካህናቱ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ፣ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ ክንድ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ ክንድ ሲሆን በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይቆማል።