2 ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሮአልና፤“ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።
3 በሬ ጌታውን፣አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤እስራኤል ግን አላወቀም፤ሕዝቤም አላስተዋለም።”
4 እናንተ ኀጢአተኛ ሕዝብ፣በደል የሞላበት ወገን፣የክፉ አድራጊ ዘር፣ምግባረ ብልሹ ልጆች ወዮላችሁ እግዚአብሔርን ትተዋል፤የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤ጀርባቸውንም በእርሱ ላይ አዙረዋል።
5 ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ?ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ?ራሳችሁ በሙሉ ታሞአል፤ልባችሁ ሁሉ ታውኮአል።
6 ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጒራችሁጤና የላችሁም፤ቍስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤አልታጠበም፤ አልታሰረም፤በዘይትም አልለዘበም።
7 አገራችሁ ባድማ፣ከተሞቻችሁ በእሳት የተቃጠሉ ይሆናሉ፤ዐይናችሁ እያየ፣መሬታችሁ በባዕድ ይነጠቃል፤ጠፍም ይሆናል።
8 የጽዮን ሴት ልጅበወይን አትክልት ውስጥ እንዳለ ዳስ፣በዱባ ተክል ወስጥ እንደሚገኝ ጐጆ፣እንደ ተከበበም ከተማ ተተወች።