4 አንቺ ሲዶና ሆይ፣አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፣ ዕፈሪ፤ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሎአልና።
5 ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣በግብፅ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።
6 እናንት በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤
7 እግሮቿ ሩቅ አገር የወሰዷት፣በዚያም እንድትሰፍር ያደረጓት፣ጥንታዊቷ የድሮ ከተማ፣የተድላ የደስ ከተማችሁ ይህች ናትን?
8 አክሊል በምታቀዳጀዋ፣ነጋዴዎቿ መሳፍንት በሆኑ፣በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፣በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?
9 የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖአል።
10 የተርሴስ ልጅ ሆይ፤ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምናእንደ ዐባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ።