1 በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንንበብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል።
2 በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤“ለመልካሙ የወይን ቦታ ዘምሩለት፤
3 እኔ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ዘወትር ውሃ አጠጣዋለሁ፤ስለዚህ ማንም አይጐዳውም፣ቀንና ሌሊት እጠብቀዋለሁ፤
4 እኔ አልቈጣም።እሾኽና ኵርንችት ምነው በተነሡብኝ!ለውጊያ በወጣሁባቸው፣አንድ ላይ ባቃጠልኋቸው!