9 እነርሱም እንዲህ ይላሉ፤ “የሚያስተምረው ማንን ነው?መልእክቱን የሚያብራራውስ ለማን ነው?ወተት ለተዉት ሕፃናት?ወይስጡት ለጣሉት?
10 በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይትእዛዝ፤በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት ነውና።
11 እንግዲያማ እግዚአብሔር፣በባዕድ ልሳን በእንግዳ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል።
12 እርሱ፣“ይህቺ የዕረፍት ቦታ ናት፤ የደከመው ይረፍ፤ይህቺ የእፎይታ ቦታ ናት” ያለው ለማን ነበር?እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም።
13 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፤በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤እዚህ ጥቂት እዚያ ጥቂት ይሆንባቸዋል።ይህ የሚሆንባቸው ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣እንዲቈስሉና በወጥመድ እንዲያዙ፣እንዲማረኩም ነው።
14 ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ፣እናንት ፌዘኞች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
15 እናንት፣ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል፤ከሲኦልም ጋር ስምምነት አድርገናል፤ውሸትን መጠጊያችን፣ሐሰትን መደበቂያችን አድርገናል፤ታላቅ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ሊነካን አይችልም” በማለት ታብያችኋል።