ኢሳይያስ 29:2-8 NASV

2 ነገር ግን አርኤልን እከባለሁ፤ታለቅሳለች፤ ዋይ ዋይ ትላለች፤ለእኔም እንደ መሠዊያ ስፍራ ትሆንልኛለች።

3 በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤በቅጥር እከብሻለሁ፤የከበባ ዐምባም ሠርቼ አስጨንቅሻለሁ።

4 ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ንግግርሽ ከትቢያ እየተጒተመተመ ይወጣል፤ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።

5 ነገር ግን ብዙ ጠላቶችሽ እንደ ትቢያ ብናኝ፣መንጋ ጨካኞችም በነፋስ እንደሚነጻገለባ ይሆናሉ።ድንገት ሳይታሰብም፣

6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በነጐድጓድ፣ በምድር መናወጥና በታላቅ ድምፅ፣በዐውሎ ነፋስና በኀይለኛ ሞገድ ፈጽሞ በሚባላም የእሳት ነበልባል ይመጣል።

7 አርኤልን የሚወጋ የአሕዛብ ሁሉ መንጋ፣በእርሷና በምሽጓ ላይ አደጋ የሚጥልና የሚከባት፣እንደ ሕልምበሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናል።

8 የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ዐድሮ፣ነገር ግን ሲነቃ ራቡ እንዳልለቀቀው፣የጠማውም ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ዐድሮ፣ነገር ግን ሲነቃ እንደ ዛለና ጥማቱም እንዳልተወው፣የጽዮንን ተራራ የሚወጋ፣የአሕዛብ መንጋ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።