15 ሕዝቤን በችግር ስታደቁት፣የድኾችንም ፊት በሐዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?”ይላል ጌታ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ዐንገታቸውን እያሰገጉ፣በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤እየተቈነኑ በመራመድ፣የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
17 ስለዚህ፣ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይቈረቈር ያመጣል፤ እግዚአብሔርም ራሳቸውን ቡሀ ያደርጋል።
18 በዚያም ቀን ጌታ የክብር ጌጣቸውን ይነጥቃቸዋል፤ የእግር አንባሩን፣ የጠጒር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን የዐንገት ጌጥ፣
19 የጆሮ ጒትቻውን፣ የእጅ አንባሩን፣ የፊት መሸፈኛውን፣
20 የራስ መሸፈኛውን፣ ዐልቦውን፣ ሻሹን፣ የሽቶ ብልቃጡን፣ አሸንክታቡን፣
21 የጣት ቀለበቶችንና የአፍንጫ ቀለበቶችን፣