ኢሳይያስ 30:16-22 NASV

16 ደግሞም ‘አይሆንም፣ በፈረስ እንሸሻለን’ አላችሁ፤ስለዚህ ትሸሻላችሁ።ደግሞም፣ ‘በፈጣን ፈረስ እናመልጣለን’ አላችሁ፤ስለዚህ አሳዳጆቻችሁም ፈጣን ይሆናሉ።

17 በተራራ ዐናት ላይ እንደ ተተከለ ሰንደቅ ዐላማ፣በኰረብታም ላይ እንደ ቆመ ምልክት፣ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስበአንድ ሰው ዛቻ፣ሺህ ሰው ይሸሻል፤በአምስት ሰው፣ሁላችሁ ትሸሻላችሁ።”

18 እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሣል፤ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሣል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና፣እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁት የተባረኩ ናቸው።

19 በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም። ለርዳታ ወደ እርሱ ስትጮኹ እንዴት ምሕረት አያደርግላችሁ ጩኸትህን እንደሰማም ፈጥኖ ይመልስልሃል።

20 ጌታ የጭንቀት እንጀራና የመከራ ውሃ ቢሰጥህም፣ አስተማሪህ ከእንግዲህ አይሰወርብህም፤ ዐይኖችህም አስተማሪህን ያያሉ።

21 ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።

22 ከዚያም በብር የተለበጡትን ጣዖቶችህንና በወርቅ የተለበዱ ምስሎችህን ታዋርዳለህ፤ “ከዚህ ወግ” ብለህም እንደ መርገም ጨርቅ ትጥላቸዋለህ።