14 የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋር አብረው ይሆናሉ፤በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ።
15 ጒጒት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿትታቀፋቸዋለች፤ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።
16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ የሚለውንተመልከቱ፤ አንብቡም፤ከእነዚህ አንዱ አይጐድልም፤እያንዳንዷም አጣማጇን አታጣም፤ይህ ትእዛዝ ከአፉ ወጥቶአል፤መንፈሱ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋልና።
17 ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች።ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል።