ኢሳይያስ 34:9-15 NASV

9 የኤዶም ምንጮች ሬንጅ፣ዐፈሯ የሚቃጠል ድኝ፣ምድሯም የሚንበለበል ዝፍት ይሆናል።

10 እሳቷ ሌሊትና ቀን አይጠፋም፤ጢሷም ለዘላለም ይትጐለጐላል፤ከትውልድ እስከ ትውልድ ባድማ ትሆናለች፤ማንም በዚያ ዳግም አያልፍም።

11 ጭልፊትና ጃርት ይወርሷታል፤ጒጒትና ቍራም ጐጆ ይሠሩባታል።እግዚአብሔር በኤዶም ላይ፣የመፈራረሷን ገመድ፣የመጥፊያዋንም ቱንቢ ይዘረጋል።

12 መሳፍንቷም መንግሥት ተብለው ለመጠራት የሚያስችላቸው ነገር አይኖራቸውም፤አለቆቿም በሙሉ ጥርግ ብለው ይጠፋሉ።

13 በቅጥር የተመሸጉ ከተሞቿን እሾኽ፣ምሽጎቹንም ሳማና አሜከላ ይወርሷቸዋል፤የቀበሮዎች ጒድጓድ፣የጒጒቶችም መኖሪያ ትሆናለች።

14 የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋር አብረው ይሆናሉ፤በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ።

15 ጒጒት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿትታቀፋቸዋለች፤ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።