1 አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ይላል አምላካችሁ።
2 ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ዐውጁላትም፤በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቶአል፤የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሎአል፤ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።
3 የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤“የእግዚአብሔርን መንገድ፣በምድረ በዳ አዘጋጁ፤ለአምላካችን አውራ ጐዳና፣በበረሓ አስተካክሉ።
4 ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፤ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ወጣ ገባው ምድር ይስተካከላል፤ሰርጓጒጡም ሜዳ ይሆናል።
5 የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፤ሰው ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።”
6 ድምፅም፣ “ጩኽ” አለኝ፤እኔም፣ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ።“ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።