ኢሳይያስ 44:2-8 NASV

2 የፈጠረህ፣ በማሕፀን የሠራህ፣የሚረዳህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ባሪያዬ ያዕቆብ፣የመረጥሁህ ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ።

3 በተጠማ ምድር ላይ ውሃ፤በደረቅ መሬት ላይ ወንዞችን አፈሳለሁና፤መንፈሴን በዘርህ፣በረከቴንም በልጅ ልጅህ ላይ አወርዳለሁ።

4 እነርሱም በለመለመ መስክ ላይ እንደ ሣር፣በወንዝ ዳር እንደ አኻያ ዛፍ ይበቅላሉ።

5 አንዱ፣ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ሌላው ራሱን በያዕቆብ ስም ይጠራልሌላው ደግሞ በእጁ ላይ ‘የእግዚአብሔር ነኝ’ ብሎ ይጽፋል፤ራሱን በእስራኤል ስም ይጠራል።

6 “የእስራኤል ንጉሥና ቤዛ እግዚአብሔር፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።

7 እስቲ እንደ እኔ ማን አለ? ይናገር፤ሕዝቤን ከጥንት ስመሠርት ምን እንደ ነበረ፣ገና ወደ ፊት ምን እንደሚሆን፣ይናገር፤ በፊቴ ያስረዳ፤ስለሚመጣውም ነገር አስቀድሞ ይናገር።

8 አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ይህን አልነገርኋችሁምን? ቀድሞስ አላሳወ ቅኋችሁምን?ለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አለን? ፈጽሞ!ወይም ሌላ ዐለት አለ? የለም! ማንንም አላውቅም።”