24 “ከማሕፀን የሠራህ፣ የተቤዠህም፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ሁሉን ነገር የፈጠርሁ፣ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ምድርን ያንጣለልሁ፣እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
25 የሐሰተኞችን ነቢያት ምልክቶች አከሽፋለሁ፤ሟርተኞችን አነሆልላለሁ፤የጥበበኞችን ጥበብ እገለባብጣለሁ፤ዕውቀታቸውንም ከንቱ አደርጋለሁ።
26 የባሪያዎቼን ቃል እፈጽማለሁ፤የመልእክተኞቼን ምክር አጸናለሁ።ኢየሩሳሌምን ‘የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ’፣የይሁዳ ከተሞችንም፣ ‘ይታነጻሉ’፣ፍርስራሻቸውን፣ ‘አድሳለሁ’ እላለሁ።
27 ጥልቁን ውሃ፣ ‘ደረቅ ሁን፤ወንዞችህን አደርቃለሁ’ እላለሁ።