6 “የእስራኤል ንጉሥና ቤዛ እግዚአብሔር፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።
7 እስቲ እንደ እኔ ማን አለ? ይናገር፤ሕዝቤን ከጥንት ስመሠርት ምን እንደ ነበረ፣ገና ወደ ፊት ምን እንደሚሆን፣ይናገር፤ በፊቴ ያስረዳ፤ስለሚመጣውም ነገር አስቀድሞ ይናገር።
8 አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ይህን አልነገርኋችሁምን? ቀድሞስ አላሳወ ቅኋችሁምን?ለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አለን? ፈጽሞ!ወይም ሌላ ዐለት አለ? የለም! ማንንም አላውቅም።”
9 ጣዖት የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች፣የሚሰሩባቸውም ነገሮች ዋጋ ቢስ ናቸው፤የሚናገሩላቸው ዕውሮች ናቸው፤ዕውቀት የላቸውም ያፍራሉም።
10 ለምንም የማይጠቅመውን አምላክ የሚቀርጽ፣ጣዖትን የሚያበጅስ ማነው?
11 ጣዖት የሚሠራ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፤እርሱና መሰሎቹም ያፍራሉ፤ሁሉም ተሰብስበው በአንድ ላይ ይቁሙ፤ይደነግጣሉ፤ ይዋረዳሉም።
12 ብረት ቀጥቃጭ መሥሪያን ይይዛል፤በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል፤ጣዖትን በመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል፤በክንዱም ኀይል ያበጀዋል።ከዚያም ይራባል፤ ጒልበት ያጣል፤ውሃ ይጠማል፤ ይደክማል።