ኢሳይያስ 45:16-22 NASV

16 ጣዖት ሠሪዎች ሁሉ ያፍራሉ፤ ይቀላሉ፤በአንድነት ይዋረዳሉ።

17 እስራኤል ግን በእግዚአብሔር፣በዘላለም ድነት ይድናል፤እናንተም ለዘላለም፣አታፍሩም፤ አትዋረዱም።

18 ሰማያትን የፈጠረ፣እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ምድርን ያበጃት፣ የሠራት፣የመሠረታት፣የሰው መኖሪያ እንጂ፣ባዶ እንድትሆን ያልፈጠራት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤‘እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

19 በጨለማ ምድር፣በምስጢር አልተናገርሁም፤ለያዕቆብም ዘር፣“በከንቱ ፈልጉኝ” አላልሁም።እኔ እግዚአብሔር እውነትን እናገራለሁ፤ትክክለኛውንም ነገር ዐውጃለው።’

20 “በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤እናንት ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ።የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።

21 ጒዳያችሁን ተናገሩ፤ አቅርቡ፤ተሰብስበውም ይማከሩ።ይህን አስቀድሞ ማን ዐወጀ?ከጥንትስ ማን ተናገረ?እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?ጻድቅና አዳኝ የሆነ አምላክ፣ከእኔ በቀር ማንም የለም፤ከእኔ ሌላ አምላክ የለም።

22 “እናንት የምድር ዳርቻ ሁሉ፣እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፤ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ።