3 እርሱም፣ “እስራኤል፤ አንተ ባሪያዬ ነህ፤በአንተ ክብሬን እገልጣለሁ” አለኝ።
4 እኔ ግን፣ “ዐላማ ሳይኖረኝ እንዲሁ ደከምሁ፤ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ነገር ጒልበቴን ጨረስሁ፤ሆኖም ግን ብድራቴ በእግዚአብሔር እጅ፣ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልሁ።
5 በእግዚአብሔር ዐይን ፊት ከብሬአለሁ፤አምላኬ ጒልበት ሆኖልኛል፤ባሪያው እንድሆን ከማሕፀን የሠራኝ፣ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ፣እስራኤልን ወደ እርሱ እንድሰበስብ ያደረገኝ፣ እግዚአብሔር አሁንም እንዲህ ይላል፤
6 እርሱም፣“ባሪያዬ መሆንህ፣የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።
7 እግዚአብሔር፣ታዳጊ የሆነው የእስራኤል ቅዱስ፣ለተናቀውና በሕዝብ ለተጠላው፣የገዦች አገልጋይ እንዲህ ይላል፤“ነገሥታት አይተውህ ይነሣሉ፤ልዑላንም አይተው፤ ይሰግዳሉ፤ምክንያቱም የመረጠህ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ነው።”
8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በወደድሁ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤በድነትም ቀን እረዳሃለሁ።ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤
9 የተማረኩትን፣ ‘ኑ ውጡ’በጨለማ ያሉትን፣ ‘ነጻ ሁኑ’ እንድትል አድርጌሃለሁ።“በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤በተራቈተውም ኰረብታ ሁሉ ላይ መሰማሪያ ያገኛሉ።