4 ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤በየማለዳው ያነቃኛል፤በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።
5 ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም።
6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢሜን ለሚነጩ ጒንጬን ሰጠሁ፤ፊቴን ከውርደት፣ከጥፋትም አልሰወርሁም።
7 ልዑል እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይአድርጌአለሁ፤እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።
8 ንጹሕ መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ በአጠገቤ አለ፤ታዲያ ማን ሊከሰኝ ይችላል?እስቲ ፊት ለፊት እንጋጠም!ተቃዋሚዬስ ማን ነው?እስቲ ይምጣ!
9 የሚረዳኝ እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤የሚፈርድብኝስ ማን ነው?እነሆ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ብልም ይበላቸዋል።
10 ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው?ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤በአምላኩም ይደገፍ።