ኢሳይያስ 54:10-16 NASV

10 ተራሮች ቢናወጡ፣ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም”ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።

11 “አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ።

12 ጒልላትሽን በቀይ ዕንቊ፣በሮችሽን በሚያብረቀርቁ ዕንቊዎች፣ቅጥሮችሽንም በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።

13 ወንዶች ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤የልጆችሽም ሰላም ታላቅ ይሆናል።

14 በጽድቅ ትመሠረቻለሽ፤የግፍ አገዛዝ ከአንቺ ይርቃል፤የሚያስፈራሽ አይኖርም፤ሽብር ከአንቺ ይርቃል፤አጠገብሽም አይደርስም።

15 ማንም ጒዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ጒዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል።

16 “እነሆ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፣የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን፣ አንጥረኛውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝአጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤