ኢሳይያስ 62:2-8 NASV

2 መንግሥታት ጽድቅሽን፣ነገሥታት ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔር አፍ በሚያወጣልሽ፣በአዲስ ስም ትጠሪያለሽ።

3 በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፣በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።

4 ከእንግዲህ፣ “የተተወች” ብለው አይጠሩሽም፤ምድርሽም፣ “የተፈታች” አትባልም፤ነገር ግን፣ “ደስታዬ በእርሷ” ትባያለሽ፤ምድርሽም፣ “ባለ ባል” ትባላለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ምድርሽም ባለ ባል ትሆናለች።

5 ጐልማሳ ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ልጆችሽ እንዲሁ ያገቡሻል፤ሙሽራ በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፣አምላክሽም በአንቺ ደስ ይለዋል።

6 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም።እናንት ወደ እግዚአብሔር አቤት፣ አቤት የምትሉ፤ፈጽሞ አትረፉ፤

7 ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት፣የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ዕረፍት አትስጡት።

8 እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሎአል፤“ከእንግዲህ እህልሽን፣ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።