8 ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤
9 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና።
10 የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆኑ፤ጽዮን ራሷ እንኳ ምድረ በዳ፣ ኢየሩሳሌምም የተፈታች ሆናለች።
11 አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣በእሳት ተቃጥሎአል፤ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል።
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ አትመለስምን?ዝም ብለህ ከልክ በላይ ትቀጣናለህን?