10 አጥብቀው ለሚፈልጉኝ ሕዝቤ፣ሳሮን የበጎች መሰማሪያ፣የአኮር ሸለቆም የከብቶች ማረፊያ ይሆናል።
11 “ነገር ግን እግዚአብሔርን ለተዋችሁት ለእናንተ፣የተቀደሰ ተራራዬን ለረሳችሁት፣‘ዕጣ ፈንታ’ ለተባለ ጣዖት ቦታ ላዘጋጃችሁት፣‘ዕድል’ ለተባለም ጣዖት ድብልቅ የወይን ጠጅ በዋንጫ ለሞላችሁት፣
12 ተጣርቼ ስላልመለሳችሁ፣ተናግሬ ስላልሰማችሁ፣በፊቴ ክፉ ነገር ስላደረጋችሁ፣የሚያስከፋኝን ነገር ስለ መረጣችሁ፣ለሰይፍ እዳርጋችኋለሁ፤ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ።”
13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ባሮቼ ይበላሉ፤እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ባሮቼ ይጠጣሉ፤እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ባሮቼ ደስ ይላቸዋል፤እናንተ ግን ታፍራላችሁ።
14 ባሮቼ፣ከልብ በመነጨ ደስታ ይዘምራሉ፤እናንተ ግን፣ልባችሁ በማዘኑ ትጮኻላችሁ፤መንፈሳችሁ በመሰበሩም ወዮ ትላላችሁ።
15 ስማችሁንም፣የተመረጠው ሕዝቤ ርግማን እንዲያደርገው ትተዋላችሁ፤ጌታ እግዚአብሔር ይገድላችኋል፤ለአገልጋዮቹ ግን ሌላ ስም ይሰጣቸዋል።
16 ስለዚህ በምድሪቱ ላይ በረከትን የሚጠራ፣በእውነት አምላክ ስም ይባረካል፤በምድሪቱ መሐላን የሚምል፣በእውነት አምላክ ስም ይምላል፤ያለፉት ችግሮች ተረስተዋል፤ከዐይኖቼም ተሰውረዋል።