21 ሰዎች ቤት ይሠራሉ፤ በውስጡም ይኖራሉ፤ወይንን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።
22 ከእንግዲህ ለሌሎች መኖሪያ ቤት አይሠሩም፤ወይም ሌላው እንዲ በላው አይተክሉም፤የሕዝቤ ዕድሜ፣እንደ ዛፍ ዕድሜ ይረዝማል፤እኔ የመረጥኋቸው፣በእጃቸው ሥራ ለረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
23 ድካማቸው በከንቱ አይቀርም፤ዕድለ ቢስ ልጆችም አይወልዱም፤እነርሱና ዘራቸው፣ እግዚአብሔር የባረከው ሕዝብ ይሆናሉ።
24 ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤ተናግረው ሳይጨርሱ እሰማለሁ።
25 ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤እባብ ትቢያ ይልሳል፤በተቀደሰው ተራራዬም፣ጒዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤”ይላል እግዚአብሔር።