1 የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤
2 “በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አይኑሩህ፤”
3 በዚህች ምድር ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ እንዲሁም ስለ እናቶቻቸው ስለ አባቶቻቸው እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤
4 “በአደገኛ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩም፤ በምድርም ላይ እንደ ጒድፍ ይጣላሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።”