22 ምክሬ ባለበት ቢቆሙ ኖሮ፣ቃሌን ለሕዝቤ ባሰሙ ነበር፤ከክፉ መንገዳቸው፣ከክፉ ሥራቸውም በመለሷቸው ነበር።
23 “እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝን?ይላል እግዚአብሔር፤“የሩቅስ አምላክ አይደለሁምን?
24 እኔ እንዳላየው፣በስውር ቦታ ሊሸሸግ የሚችል አለን?”ይላል እግዚአብሔር።“ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን”ይላል እግዚአብሔር።
25 “ ‘ሕልም አለምሁ ሕልም አለምሁ’ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩትን የነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ፤
26 ይህ ነገር፣ የገዛ ልባቸውን ሽንገላ በሚተነብዩ በሐሰተኞች ነቢያት ልብ ውስጥ የሚቈየው እስከ መቼ ነው?
27 አባቶቻቸው በኣልን በማምለክ ስሜን እንደ ረሱ፣ እነርሱ በሚነጋገሩት ሕልም፣ ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ያደረጉ ይመስላቸዋል።
28 ሕልመኛ ነቢይ ሕልሙን ያውራ፤ ቃሌ ያለው ግን በታማኝነት ይናገር፤ ገለባና እህል ምን አንድ አድርጎአቸው!” ይላል እግዚአብሔር።